ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 – 9ኛ ሳምንት
በድሬደዋ ሀገር አቀፍ ስታዲየም
ማክሰኞ ህዳር 13 2015
1:00 በተከናወነ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3ለ0 በሆነ ዉጤት ሀዋሳ ከተማን አሸንፏል።
👉 ሀዋሳ ከተማ ዐ – 3 ቅዱስ ጊዬርጊስ
⚽️06′ አማኑኤል ገ/ሚካኤል
⚽️15′ ጋቶች ፖኖም
⚽️32′ እስማኤል ኦሮ አጎሮ
አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በ6ኛው ደቂቃ ፣ ጋቶች ፓኖም በ15 ደቂቃ ኢስማኤልን ኦሮ አጎሮ በ32 ኛው ደቂቃ የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ባህሩ ነጋሽ በጨዋታው የፍፁም ቅጣት ምት አድኗል።
የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ኢስማኤልን ኦሮ አጎሮ
አስር ጎሎችን በማስቆጠር የ2015 አ/ም የሊጉን ከፍተኛ ጎል አግቢነቱን በበላይነት እየመራ ይገኛል።
በ10ኛው ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወላይታ ድቻ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን የሚጫወቱ ይሆናል።