አዲስ አዳጊዎቹ ፉልሀሞች ሊቨርፑልን ነጥብ አስጣሉ
አዲስ አዳጊዎቹ ፉልሀሞች ሊቨርፑልን ነጥብ አስጣሉ
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዛሬ ከአዲስ አዳጊው ሊቨርፑል ጋር ባደረጉት ጨዋታ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።
በ2023/23 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለዋንጫ ፉክክር የሚጠበቁትና ባሳለፍነው አመት ከሻምፒዮኖቹ ማንቸስተር ሲቲዎች በአንድ ነጥብ ዝቅ ብለው የጨረሱት ቀያዮቹ ሊቨርፑሎች የውድድር አመቱን በአቻ ውጤት ጀምረዋል ።
ጨዋታው በተጀመረ 35 ኛው ደቂቃ የፉልሀሞች ወሳኝ አጥቂ የሆነው ሚትሮቪች ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው በአዲስ አዳጊዎቹ ፋልሀሞች አንድ ለዜሮ መሪነት እስከ 64ኛው ደቂቃ ድረስ እንዲቆይ አስቻለ ። 64ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው አዲሱ የሊቨርፑል ፈራሚ ዳርዊን ኑኔዝ ግብ አስቆጥሮ ሊቨርፑላዊያንን አቻ አደረገ ።
ብዙም ሳይቆይ በ71ኛው ደቂቃ ፉልሀሞች ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ልማደኛው ሚትሮቪች አስቆጥሮ ደግም ፉልሀሞችን መሪ ቢያደርግም የፋልሀሞች መሪነት መዝለቅ የቻለው ለ10 ደቂቃዎች ያክል ነበር ። በ81ኛው ደቂቃ ግብፃዊው ሞሀመድ ሳላህ አስቆጥሮ ሊቨርፑልን አቻ አደረጎ ጨዋታው 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል ።
ኡራጋያዊው ዳርዊን ኑኔዝ በሊቨርፑል ቤት የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ግብ ማስቆጠር ችሏል ።
ሀሳብ አስተያየትዎን ይለግሱን
በፈቃደኝነት ላይክ ሼር ኮሜንት ያድርጉ እናመሰግናለን ።
Ananiya Feleke