ሠማያዊዎቹ የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል ።
ሠማያዊዎቹ የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል ።
የመጀመሪያ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር በጉዲሰን ፓርክ ቼልሲዎች የውድድር አመቱን በድል ጀምረዋል ።
ጨዋታው በተጀመረ በ18ኛው ደቂቃ የኤቨርተኑ ቤን ጎድፍሬይ ባስተናገደው ከባድ ጉዳት በሆልጌት ተቀይሮ ወጥቷል ። የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 1 ደቂቃ ሲቀረው የኤቨርተን የመሀል ተጫዋች የሆነው ዶኩሬ በቤን ቺልዌል ላይ በሰራው ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ለቼልሲ ተሰጥቶ ፍፁም ቅጣት ምቱን ልማደኛው ጆርጊኒሆ አስቆጥሮ ጨዋታው አንድ ለ ዜሮ በሆነ ውጤት ተጠናቋል ።
የአሠልጣኝ ፍራንክ ላምፓርዱ ክለብ ኤቨርተኖች ባሳለፍነው አመት እስከ መጨረሻዎቹ 2 ጨዋታዎች ድረስ የመውረድ ስጋት ውስጥ እንደነበሩ ይታወሳል ታዲያ የኤቨርተን ደጋፊዎችም ሆነ አመራሮች የአምናውን ውጤት በዘንድሮ አመት የመመልከት ፍላጎት የላቸውም ።
የዚህን ክለብ ውጤት ለማሻሻል እና በፕሪሚየር ሊጉ ተፎካካሪ ለማድረግ እንደ ማክ ኒል እና ታርኮውስኪ የመሳሰሉ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመው ነው የውድድር አመቱን የጀመሩት ።
የቶማስ ቱሄሌቹ ቼልሲዎች በበኩላቸው ባለፋት 4 እና 5 ዓመታት በሊቨርፑል እና በሲቲ ተወስዶ የነበረውን የሻምፒዮንነት ፉክክር ወደ ለንደን ማምጣት ይፈልጋሉ ።
በአዲሱ የክለቡ ባለቤት ቶድ ቦህሊ አማካኝነት ትላልቅ ዝውውሮችን ጨርሰው ክለቡን ይበልጡኑ ለማጠናከር የሚሰሩት ቼልሲዎች በዝውውር መስኮቱ በርካታ ነባር ተጫዋቾቻቸውንም አጥተዋል ።
አንቶኒዮ ሩደገርን ለሪያል ማድሪድ አሳልፈው የሰጡት ቼልሲዎች በምትኩ ጠንካራውን እና በበርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ሲፈለግ የነበረውን ካሊዶ ኩሊባሊን አስፈርመው ዛሬ በጉዲሰን ፓርክ የቋሚነት እድል ሠጥተውታል ።
በጨዋታው በቼልሲ በኩል አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ራሂም ስተርሊንግ እና ካሊዶ ኩሊባሊ በቋሚነት በመሰለፍ ለጨዋታው ድል ቁልፉን ሚና ተጫውተዋል ሌላኛው አዲሱ ፈራሚ ማርክ ኩኩሬላ በጨዋታው ተቀይሮ በመግባት ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት ችሏል ።
Ananiya Feleke