አሰልጣኝ ውበቱ አባተም ዝግጅታቸውን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

በሀገር ውሰጥ ሊግ ብቻ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚደረገው የቻን ውድድር በአልጄሪያ በቀጣይ አመት በጥር ወር ይከናወናል ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር በመጪው አርብ በታንዛኒያ ጨዋታውን የሚያደርግ ያከናውናል ።

ብሄራዊ ቡድኑ በአዳማ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ዝግጅቱን በማድረግ ነገ ወደ ዳሬ ሰላም ይጓዛል
አሰልጣኝ ውበቱ አባተም ዝግጅታቸውን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን
ለ23 ተጫዋቾችን ጠርተዋል።
<<ጫና ካለበት ወድድር ነው የመጡት የማገገም እና ታክቲካል ስራዎች እንዲሰሩ በማድረግ ሰርተናል
ከተጠሩት መካከል አማኑኤል መጠነኛ ጉዳት ነበረበት ዳዋና በዛብህ መለዮ ደግሞ ከጡንቻ መሳሳብ ጋር የተያያዘ መጠነኛ የህምም ስሜት ከመፈጠሩ ውጪ ሌሎች ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተጋጣሚውን ደቡብ ሱዳንን በተመለከተ ሰፊ የሆነ መረጃ ማግኘት አልቻልኩም በዕርግጥ ከሰኔ 28 ጀምሮ ልምምድ እንደጀመሩ መረጃው አለን ። ቀደም ብለው አስበውበት እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቄአለሁ ። ጨዋታውን አሸንፈን ለማለፍ በቂ ዝግጅት አድርገናል ።
ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ።
ያሉን ቀኖቹ አጭር ናቸው ስለዚህ ልጆቹን ከውድድር ወደ ውድድር መልሰህ መክተት አንዱ አስቸጋሪ ነው ። ሁለተኛው ነገር አዕምሮአቸው ያልተረጋጋ ልጆች ከፊርማ ጋር ተያይዞ ወደ እዛም ወደ እዚም ብዙ ውጣ ውረዶች አሉ

ከውድድር ወደ ሌላ ውድድር መሄዱ አድካሚ ነው ተጫዋቾቻን ደግሞ እንደዚህ አይነቱን ድካም የመቋቋማቸው ነገርም አስቸጋሪ ቢሆንም ቻን ለሀገራችንም ለተጫዋቾችም ለእግር ኳስ ቤተሰቡም ሌላ ዕድል ይፈጥራል ። አፍሪካ ዋንጫ መግባት ችለናል በዛ ውድድር ላይ የጀመርነው መንገድ አለ አሁን ደግሞ በቻን ውድድር ቢያንስ ለአልጄሪያው ውድድር ለማለፍ ደግሞ ሌላ ዝግጁነት እንዲኖራቸው ዕቅድ ይዘን እየሰራን ነው ። እንግዲህ ከባድ ነው ደቡብ ሱዳን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ያለችበትን ደረጃ ለማየት ሞክረናል ። ከሞሪታንያ ከማሊ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎቿን አይተናል ግን ያ ቡድን አይደለም የቻን ውድድር ላይ የሚመጣው በግማሽ ደረጃ የሚደርሱ አዲስ ልጆች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምታለን ። በይበልጥ ያተኮርነው በራሳችንን ቡድን የጀመርነውን ለውጥ አጠናክሮ የመቀጠል ላይ እና ተጋጣሚያችን ሊመጣ ይችላል ብለን በምናስበው ነገር ላይ ለመዘጋጀት ሙከራ ከማድረግ ሌላ አማራጭ ግን የለንም ። እነሱ
እሰራኤል ፤ አውስትራሊያ ፤ ኡጋንዳ ፤ ኬንያ የሚጫወቱ ልጆች አሏቸው ስለዚህ እነዛ ልጆች እዚህ ውድድር ላይ አይካፈሉም ። ቢያንስ ቢያንስ ግን ምን አይነት ጨዋታ ሊጫወቱ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል
ኮንትራቴ የሚያበቃው መስከረም መጀመሪያ ላይ ነው ። እንዳለመታደል ሆኖ በኛ ሀገር እንደዚህ አይነት ነገር አልተለመደም ኮንትራት የሚጠናቀቅበት ቀኗን ነው እንጂ ያየነው ቀጣይ ኮንትራት ግን በክለብም ይሁን በተጫዋቾችም ይሁን በአሰልጣኞች የመጨረሻዋ ቀን ነው የምትጠበቀው ። ቢያንስ 3 ወር ወይም 6 ወር ሲቀረው ንግግር ቢኖር የሚመጡ አለመረጋጋቶችን ይቀንሳል ስለዚህ ከፌዴሬሽኑ ጋር ንግግር ጀምረናል ። በሁለታችንም በኩል ጥሩ ነገር አለ ዝርዝር በሆኑ ነገሮች ላይ ግን ማውራት ይጠበቃል >>ብለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published.