ጀግኖቹ አትሌቶቻችን ዛሬም በድጋሚ ሀገራቸውን ወክለው ይሮጣሉ ።

በኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት ሀገራችን አንድ የፍፃሜ ውድድርን እና ሁለት ማጣርያዎችን ታደርጋለች ።

ሌሊት 8:25 የሴቶች 5,000 ሜትር ማጣርያ ሲደረግ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ለተሰንበት ግደይ እና ዳዊት ስዩም ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው

ሌሊት 9:20 ሲል ደግሞ በወንዶች 800 ሜትር ማጣርያ ይደረጋል በውድድሩም ኤርሚያስ ግርማ እና ቶሎሳ ቦደና በኢትዮጵያ በኩል የሚሰለፋ አትሌቶች ናቸው ።

ከቀናት በፊት ለኢትዮጵያ 1500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያመጣችው እና በ5000 ሺ ሜትር በተጠባባቂነት ተይዛ የነበረችው ጉዳፍ ፀጋዬ በአትሌት በእጅጋየሁ ታየ ምትክ ትሮጣለች ።

ሌሊት 11:45 ላይ የሴቶች 3,000 ሜትር መሰናል ፍፃሜ የሚደረግ ሲሆን መቅደስ አበበ እና ወርቅውሃ ጌታቸው 4ኛውን ወርቅ ወደ ሀገራቸው ለማስገባት የሚፋለሙ አትሌቶች ናቸው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.