ዋልያዎቹ ከ 8 አመት በኋላ በአፍሪካ መድረክ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሽንፈት ጀመሩ።

▪️ትላንት በተጀመረው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ያካሄደ ሲሆን በኬፕቨርድ ብሄራዊ ቡድን 1-0 ተሸንፈዋል።ከዚ ጨዋታ ቀደም ብሎ በመክፈቻ ጨዋታው ካሜሩን ብርቱ ፉክክር ከቡርኪናፋሶው ቢያጋጥመውም በቪንሰንት አቡበከር 2 የፍፁም ቅጣት ምት ግቦች ታግዛ  ማሸነፍ ችላለች። ይህ ጨዋታ ከመጠናቀቁ በኋላ የጀመረው የኢትዮጵያ እና የኬፕቨርድ ጨዋታ በኦሎምቤ ስታዲየም ሲካሄድ ዋልያዎቹ አጀማመራቸው ጥሩ ቢሆንም 12ኛው ደቂቃ ላይ አስቻለው ታመነ ወደኋላ የመለሰውን ኳስ ያሬድ ባየህ መቆጣጠር ሳይችል ቀርቶ አጥቂው ሁሊዮ ታቫሬዝ ላይ በሰራው ጥፋት ጨዋታውን ሲመሩ የነበሩት አንጎላዊው ሄልደር ማርቲንስ  V.A.R ካዩ በኋላ ቀይ ካርዱን መዘዋል።ኢትዮጵያም ቀሪውን 78 ደቂቃ  በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ ተገዳለች።

▪️አሰልጣኝ ውበቱ አባተም ወዲያውኑ መስኡድ መሀመድን በተከላካዩ ምኞት ደበበ ተክተው ጨዋታውን ቀጥለዋል። በተለምዶው የአቶ ውበቱ አባተ አጨዋወት አጭር ቅብብል ላይ የተመሰረተ ቢሆንም በጊዜ ቡድኑ ቀይ ካርድ ማየቱ ይህንንም እንዳይተገብር ትልቅ እንቅፋት ሆኖበታል። 72% በራሳቸው የሜዳ ክልል ውስጥ ለመቀባበል ሲገደዱ በአንፃሩ ኬፕቨርድ 84% የተሳኩ የኳስ ቅብብሎችን ማሳካት ችለው ነበር።የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ተጠናቆ በተጨመረው 1 ደቂቃ ላይ ለሳውድ አረቢያው አል-ፋይሳሊ ሚጫወተው ዩሊያ ታቫሬስ ከ ጋሪ ሜንዴዝ ሮድሪጌዝ የተሻገረለትን ኳስ በቴስታ አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።

ከእረፍት መልስ ከዚች ጎል መቆጠር በኋላም ያን ያክል አስደንጋጭ ሙከራ በሁለቱም ቡድኖች መሀከል ተደርጎል ማለት አይቻልም። የኬፕቨርድ ብሄራዊ ቡድን የቁጥር ብልጫቸውን በመጠቀም switch of play ወይም ኳስ በረጅሙ ከቀኝ መስመር ወደ ግራ እንዲሁም ከግራ መስመር ወደ ቀኝ መስመር እያንሸራሸሩ ተጠምደው ነበር 45 ደቂቃውን ያሳለፉት በአንፃሩ ብሄራዊ ቡድናችን በሁለተኛው አጋማሽ ተከላክሎ ፣ አፈግፍጎ ይጫወታል ቢባልም ተጭነው ባይጫወቱም ጥንቃቄ ላይ አመዝነው እና በአጭሩ እየተቀባበሉ ከኬፕቨርድ ፕሬሲንግ ሲወጡ የነበረበት መንገድ ሚበረታታ እና ይበል የሚያሰኝ ነው። ሙጅብ ቃሲም ፣ በዛብህ መለዮ ፣ ፍፁም አለሙ እና ፍሬው ሰለሞንን ቀይረው ቢያስገቡም 1 ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ እንኳን ማድረግ ተስኖታል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ የፊታችን ሀሙስ አስተናጋጇን ካሜሮንን ምሽት 1:00 ላይ በኦሌምቤ(ስታዲየም) የምትገጥም ይሆናል። እዛ ጨዋታ ላይ ብሄራዊ ቡድኑ ምን የተለየ ነገር ይዞ ይቀርባል ምን አይነት ነገርስ ያሳየናል ሚለውን ሀሙስ ምሽት 1:00 መልስ ምናገኝበት ሰአት ነው።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.