የ እለተ ረቡዕ አጫጭር ስፓርታዊ መረጃዎች

የ እለተ ረቡዕ አጫጭር ስፓርታዊ መረጃዎች

 

▪️ትላንት በተደረገው የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ረፋድ ላይ ሰበታ ከነማን ከ ድሬዳዋ ከነማ ሲያገናኝ በሰበታ ከነማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ከሰአት 9:00 ላይ ሀዋሳ ከነማ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ጨዋታቸውን አከናውነው በ ሀብታሙ ታደሰ የ 76 ደቂቃ ብቸኛ ግብ ሀድያ ሆሳዕና አሸናፊ መሆን ችሏል።
▪️በዚህም መሠረት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ 1 ጨዋታ እየቀረው ሰበታ ከነማ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
▪️15ኛው የ አዲስአበባ ሲቲ ካፕ ውድድሮች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ።
የ አዲስአበባ ቢቂላ ስታዲየም ምሽት ጨዋታዎችን ማስተናገድ ስለማይችል ጨዋታዎቹ ቀደም ተብለው እንዲካሄዱ ተወስኗል።በዚህም መሠረት
7:00 ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ሚገኘው
ጅማ አባ ጅፋር ከ ባህርዳር ከነማ እንዲሁም 9:00 ሲል ቅ/ጊዮርጊስ ከ መከላከያ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
ከውጭ
▪️ ማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመፈለግ እንደማይቸኩል እና ለ ኦሌ ድጋፋቸውን እንደሚሠጡት ገልፀዋል። የ ማንቸስተር ዮናይትድ ደጋፊዎች ኦሌ በሚያደርጋቸው የ ተጫዋች ቅያሪዎች እንዲሁም ጨዋታውን የመምራት ብቃታቸው ላይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ያነሳሉ ቀያዮቹ ሰይጣኖች በ ፕሪሚየር ሊጉ በ አስቶን ቪላ ጋ ሽንፈት ሲቀምሱ ከ ኤቨርተን ጋር ነጥብ መጋራታቸው ሚታወስ ነው።
▪️የ ሎስ ብላንኮዎቹ ፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ የ ፒ.ኤስ.ጂው ኪሊያን ምባፔ በ ጥር ዝውውር ክለባቸውን እንደሚቀላቀል ፍንጭ ሰተዋል።ኪሊያን ምባፔም ቢሆን ከ ሌ.ኪ.ፕ ጋዜጣ ጋር በነበረው ቃለምልልስ “ከዚህ ክለብ ከወጣሁ ምሄደው ሪያል ማድሪድ ብቻ ነው ግን ለፒ.ኤስ .ጂ ክለብ እና ለደጋፊው ትልቅ ክብር አለኝ እነሱ ሚሉትን ውሳኔ አከብራለሁ እንድለቅ በተፈቀደልኝ ሰአት ላይ ክለቡን እሰናበታለሁ” ማለቱ ይታወሳል።

#ሚካኤል_ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published.