ለናይጄሪያ መጫወት ይችሉ የነበር ተጫዋቾች

 

ለናይጄሪያ መጫወት ይችሉ የነበር ተጫዋቾች

ዳቪድ አላባ

በኦስትሪያ ቪዬና የተወለደው ይህ ድንቅ ተጫዋች ምንም በዛ ይወለድ እንጂ ዘሩ ከ ናይጄሪያ የሚመዘዝ በመሆኑ ለናይጄሪያ መጫወት ይችል ነበር ፡፡የባየርን ሙኒኩ ኮከብ ለሚጫወትላት ሀገርም ትልቅ አስተዋጽኦን አድርጓል በ2016ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገዋልም፡፡

ዴሊ አሊ

የቶተንሀሙ ኮከብ ዴሊ አሊ ምንም እንኳን በጊዜው ጥሩ አቋም ላይ ባይገኝም የፕሪምየር ሊጉ የአመቱ ወጣት ተጫዋች መሆን ጭምር ችሎ ነበር እንግዲህ ይህም ኮከብ ናይጄሪያን መወከል ይችል ነበር፡፡

ጋቢ ግቦላሆር

ጋቢ ለናይጄሪያ ትልቅ ጥቅም ይሰጥ ነበር በጊዜው ግን ሊሆን አልቻለም ለተጫወተላ እንግሊዝም 3 ጊዜ ብቻ ነው ተሰልፎ መጫወት የቻለው በሱም ምንም ጎል ማስቆጠር አልቻለም ለናይጄሪያ ቢሰለፍ ኖሮ ትልቅ ነገርን መበርከት ሚችል ነውጠኛ ተጫዋች ነበር በፕሪምየር ሊጉ ለአስቶን ቪላ 13 አመታት አገልግሎ በ341 ጨዋታዎች 75 ጎሎችን ማስቆጠር በመቻል ትላቅ እምቅ አቅም እና ችሎታ የነበረው ተጫዋች ነበር

ሮዝ ባርክሌይ

ተጫዋቹ ምንም ገጽታውን ስናየው አፍሪካዊ ዝርያ ያለው ባይመስልም አያቱ ናይጄሪያዊ ናቸው በሊቨርፑል የተወለደው ይህ እንግሊዛዊ አባቱም ናይጄሪያዊ ዝርያ ናቸው የሊቨርፑል ነዋሪ ይሁኑ እንጂ ፒተር ኢፋንጋ የተባሉት አባትየው ጋር ጥሩ ግንኙነት የሌለው ሮዝ ባርክሌይ ስሙም በዛ ሚጠራው በእናቱ ስም ባርክሌይ ነው፡፡

ቡካዮ ሳካ

በአርሰናል ቤት አስደናቂ አቋም እያሳየ ሚገኘው ታዳጊ ቡካዮ ሳካ አዲሱ የዚህ ዝርዝር አባል የሆነ ተጫዋቸወ ነው ፡፡ ለእንግሊዝ ከ16 አመት በታች ጀምሮ እዚህ የደረሰው ሳካ ለዋናው ቡድን 4ዚዜ ተሰልፎ መጫወት ችሏል፡፡ሁለቱም ቤተሰቦቹ ከናይጄሪያ ለስራ የመጠ ሲሆኑ ቡካዮ በእግር ኳስ ሂወቱ  አባቱ ትላቅ ቦታ እንዳላቸው ይገልጻል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.