ዝላታን ተመልሶ ሊመጣ ነው

ዝላታን ተመልሶ ሊመጣ ነው

በኢሮፓ ሊግ ምድብ ድልድል ማንችስተር ዩናይትድ ከኤሲ ሚላን ተደለደሉ ማንችስተር ዩናይትድ ከባድ ተጋጣሚ በእጣው ወቶለታል የቀድሞ የፊት መስመር ተጫዋቻቸው ዝላታን ኢብራሂሞቪችም የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል፡፡የ39 አመቱ አጥቂ ማንችስተር ዩናይትድ በ2017 በጆዜ ሞሪንሆ እየተመራ ዩሮፓ ሊጉን እንዲያሸንፉ ትልቂ ሚናን ተጫውቷል፡፡ኤሲሚላንንም በውድድር አመቱ ለሴሪአው ተፎካካሪ እንዲሆኑ አነቃቅቷቸዋል አሁንም ዋንጫውን ሊያነሱ ኢንተር ሚላን እና ጁቬንቱስን እያጨናነቁ ነው ፡፡ኦሊጉናር ሶልሻየርም ዋንጫ ማንሳት ትልቁ እቅዱ ነው ክለቡን ማሰልጠን ከጀመረ ቡድኑ አሁን ያለበትን አይነት ጥሩ አቋም አላሳየም፡፡

ዝላታን በ2016-2018 ማንችስተር ዩናይትድ በቆየበት ጊዜ በ53 ጨዋታዎች ተሰልፎ ሲጫወት 29 ግቦችን ማስቆጠር ችሎ ነበር ፡፡ከዝላታን ኢብራሂሞቪች ባሻገር እንደነ ዴቪድ ቤካም እና ያፕ ስታም ስታም የመሳሰሉ እውቅ ተጫዋቾች የሁለቱም ቡድኖች መለያ ለብሰው ተጫውተዋል፡፡

ክለቦቹ የድሮዎቹ ሀያላን ሊያስብል በሚያስችል መልኩ በአውሮፓ የነበራቸውን ንግስና ከተነጠቁ ቆይተዋል ከነበሩበት የከፍታ ማማ ላይ ለአመታት ሲንከባለሉ ቆይተዋል፡፡በጊዜአቸው ዩሮፓ ሊግ ራሱ አይመጥናቸውም ነበር አሁን ግን ጊዜ ጥሏቸው ክብራቸውን በሌሎች ተነጥቀው ይገናኛሉ፡፡

ግን ዘንድሮ በሁለቱም ላይ ለውጥ ታይቷል የየሊጎቻቸውንም ደረጃ ሰንጠረዥ መርተው ነበር አሁንም ሁለቱም በየሊጋቸው  ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ዋንጫውን ሊያለሱት ነው እንዴ ተብሎም ተገምቶ ነበር ሁለቱም በከተማ ተቀናቃኞቻቸው ቦታቸውን ከመነጠቃቸው በፊት ፡፡

 

ቢሆንም ይህ ጨዋታ ሀያላኑን ከወደቁበት ከፍ የማድረግ አቅም አለው ለፍጻሜ መድረስ ብቻ ሳይሆን ማሸነፍ ለሁለቱም አስፈላጊ ነው ዋንጫ ከራቃቸው ቆይቷል፡፡ኢብራ ኤሲሚላንን እንዳነቃቃው በማንችስተር ቤትም የክለቡን ስሜት እና ውጤት ያነሳሳው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ይገኛል ይህ ተጫዋች የክለቡ አከርካሪ እንደሆነ ቀጥሏል  ይሄ ተጫዋች በፕሪምየር ሊጉ ብቻ 39 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቶ 23 ጎሎችን እና 13 ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡አነዚህን ተጫዋቾች መርጠን ጠቀስን እንጂ በአጠቃላይ ሁለት በወጣቶች እና ልምድ ባላቸው ተጫዋቾቻቸው እየታገዙ የነበሩበት ክብር ላይ ለመመለስ ሚታገሉ ቡድኖች ናቸው በወጣቶች በሁለቱ ክለቦች ብዙ ተስፈኞች ይገኛሉ ለአብለት ያህል ግሪን ዉድ ፤ ራፋኤል ሊያዎ ፤ ብራሂም ዲያዝ ፤ ማርከስ ራሽፎርድ ፤ አማድ ዲያሎ ፤ ዲን ሄንደርሰን ፤ ጂያሉጂ ዶናሩማ ጥቂቶቹ ናቸው ፡፡

የሁለቱ ግጥሚያም የመጀመሪያው ጨዋታ

ኦልድ ትራፎርድ ላይ መጋቢት 2

የመልሱ ጨዋታ ደግሞ መጋቢ 9 ሳንሲሮ ላይ የደረጋል

Leave a Reply

Your email address will not be published.