ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት የዲሲፒሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉጨዋታዎችን  ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።

በ11ኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች14 ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ።
የ ኢትዮጵያው ቡናው አቡበከር ናስር በዚህኛው ሳምንት ብቸኛው ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት የቻለው ተጫዋች ሲሆን የጅማ አባ ጅፋሩ ተመስገን ደረሰ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚ ተጫዋቾች ናቸው ።

በ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች18 ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 280 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በ አስራ አንደኛው ሳምንት ጨዋታዎች የቀይ ካርድ የተመለከተ አንድም ተጫዋች ሳይኖር ያለፈበት ሳምንትም ሆኖ አልፏል ።

የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ጥር 29፣ 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ

1. አቶ ወንድሙ ብሩ (የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ) ቅዳሜ ጥር 22፣ 2013 ዓ. ም ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ10ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በዕረፍት ሰዓት የዕለቱ ጨዋታ ታዛቢ የተቀመጡበት ቦታ በመምጣት ጨዋታውን በመሩት ዳኞች ዙሪያ አፀያፊ አስተያየት መስጠታቸው በጨዋታው ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል። የቡድን መሪው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 6/ስድስት/ ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ወስኗል።

የአስራ ሁለተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጰያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከመጪው አርብ ሳምንት  ጀምሮ በተጠባቂ መርሀ ግብሮች በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.