የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ወሳኝ ውጤቶች

በሳምንቱ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብሮች የተለያዩ ወሳኝ ጨዋታዎች ሲደረጉ የሊጉ መሪዎች ማንቸስተር ሲቲዎች አርሰናልን 1-0 በማሸነፍ መሪነታቸውን እንደያዙ ቀጥለዋል በጨዋታው ኬቨን ዴብራይን ወደ ሜዳ ተመልሶ ተጫውቷል መሀል ሜዳው ላይም ኢካይ ጉንዶጋን ፈርናንዲንሆ እና በርናርዶ ሲልቫ ተጣምረው ታይተዋል።

ከጨዋታው በኃላም የአርሰናሉ አለቃ ሚካኤል አርቴታ ጎል ፊት ለፊት ጥራት እና ጨራሽ አጥተን ነበር ሲል ገልጿል። ጄሚ ሬድናፕም እንደሚለው ፒየር-ኤሚሪክ ኦባሜያንግ አልፎበታል እና በእያንዳንዱ ጨዋታ ውስጥ ጫና መቋቋም አልቻለም ጋቦናዊው አጥቂ ባለፈው የውድድር አመት በሁሉም ውድድሮች 29 ግቦችን በማስቆጠር በመስከረም ወር እራሱን በሳምንት 350,000 ፓውንድ የሚያስገኝ አዲስ ኮንትራት ያገኘ ሲሆን በዚህ የውድድር ዘመን ግን ያንን ማስጠበቅ አልቻለም::

ተጋጣሚው እና የቀድሞ የሚካኤል አርቴታ የስራ አለቃ የኢትሀዶቹ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አንዳንዴ 1-0 ማሸነፍ ጥሩ ነው ይህም ለተጫዋቾች ምን ያህል ፉክክሩ ከባድ እንደሆነ ያሳያቸዋል ብሏል።ራሂም ስተርሊንግ በግንባር ተገጭቶ የገባው ግብ ጨዋታውን አሸንፈው እንዲወጡ ሲረዳቸው ድሉም በሁሉም የውድድር መድረክ 18ኛ ተከታታይ ድላቸው ነው።አርሴናል በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሜዳቸው ሀያ አንድ ነጥቦችን ጥለዋል መድፈኞቹ በሜዳቸው ከ ሲቲ ጋር ባደረጉት አራት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎችግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል ::

 

በሌላ ጨዋታ ኦልድትራፎርድ ላይ ኒውካስትልን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 3-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል ጎሎቹም ከማርከስ ራሽፎርድ ዳንኤል ጄምስ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ የተገኙ ሲሆን ሴንት ማክሲሚን የኒውካስትሎችን ማፅናኛ አስቆጥሯል። ኦሊጉናር ሶልሻየር ዳንኤል ጄምስን አድንቋል  ተጫዋቹ በ3 ጨዋታ 3ጎሎችን አስቆጥሯል:: ኦሌ የዋንጫ ፉክክሩ አላበቃም ይላል ” እስኪያልቅ ድረስ ተፈፅሟል አልልም በጭራሽ “እዚያ ፉክክር ዉስጥ ፣ መስራታቸውን ቀጠለው ውጤት ያገኙ ብዙ ምሳሌዎችን አይተናል ሲልም ተስፋ እንዳላቸው ገልጿል::ስቲቭ ብሩስ ቡድኔ አይወርድም ፉል ሀም እያሸነፈ ቢሆንም ደጋፊ ስጋት አይግባው እናገግማለን ብለዋል ቡድናቸው ግን በ10 ጨዋታ 8 ሽንፈት አስተናግዷል ከወራጅ ቀጠናም 3 ነጥብ ብቻ ከፍ ብለው ነው ቁጭ ያሉት።

 

ጆዜ ሞሪምሆ እና ቶተንሀም በሊጉ ከድል ጋር ከተራራቁ ሰንባብተዋል ።በለንደን ደርቢ በዌስትሀም 2-1 ተሸንፈው ችግራቸውን አክርረውታል::ቶተንሀም ካለፉት ስድስት የሊጉ ጨዋታዎች በአምስቱ ሽንፈትን ሲያስተናግዱ አስር ጎሎች ተቆጥረውባቸዋል ።በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ላይ ሲቀመጡ አስራ አራት ጨዋታዎች ከፊታቸው እየጠበቋቸው ከ ሻምፒየንስ ሊግ ደረጃው በዘጠኝ ነጥቦች ርቀዋል ።ከማንችስተር ዩናይትድ ባሳለፍነው የጥር ዝውውር መስኮት ዌስትሀምን የተቀላቀለው ጄሴ ሊንጋርድ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሶስት ግብ ማስቆተር የቻለ ሲሆን 1 ለግብ የሚሆን ኳስ ማቀበል ችሏል::

ሊቨርፑል በ ኤቨርተን ሽንፈትን ያስተናገደው ከ አስራ አንድ ዓመታት በፊት ሲሆን 3,779 ቀናት ተቆጥረዋል ።የሊቨርፑል አዲሱ ፈራሚ የመሐል ተከላካይ ኦዛን ካባክ ለ ሊቨርፑል ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች በሁሉም የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።ሊቨርፑሎች ተከታታይ አራት ጨዋታዎች በሜዳቸው ለመሸነፍ ችለዋል ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.