እግር ኳስ ንጉሷን አጣች
በአለማችን እግር ኳስ ላይ መንገስ የቻለው አርጀንቲናዊው ምትሀተኛ ዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ዛሬ አመሻሹ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ።
በርካታ የዲያጎ አርማንዶ ማራዶናን እና የብራዚላዊው ጥበበኛ ፔሌን አድናቂዎች ሁለቱን የአለም እግር ኳስ ንጉሶችን በማወዳደር ሰጣገባ ውስጥ ሲገቡ እንመለከታለን ።
የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች ከመሆኑም ባለፈ የሀገሩ አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር ነበር ይቺን አለም የተሰናበትው ።
ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ ነበር በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ሲደረግለትም ቆይቶ ነበር ።
ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በተወለደ በ60 አመቱ ነው ላይመለስ ያሸለበው ። 🕯🕯🕯