ሊቨርፑል ከ ማንችስተር ዩናይትድ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ጨዋታ

እሁድ ምሽት 1፡30

የዕርስ በርስ ግንኙነት

 • ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው የመጨረሻ 10 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንድ አጋጣሚ ብቻ ነው።
 • ሊቨርፑል ለመጨረሻ ጊዜ በሜዳው ያደረጋቸውን  3 ተከታታይ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዩናይትድን የረታው እኤአ ከ 2000-2002 ባለው ጊዜ ነበር።
 • ማንቸስተር የናይትድ በሊጉ ከባለፈው የውድድር ዘመን ጀምሮ 15 ጨዋታዎችን ከሜዳው ውጪ ያልተሸነፈ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ሽንፈትን ያስተናገደው በአሁኑ ተጋጣሚው ሊቨርፑል እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 19 2020 ላይ ነበር፡፡ እሁድ ምሽት ከጨዋታው ነጥብ ይዞ መውጣት ከቻለ ለ 1 ድፍን አመት ሙሉ በሊጉ ከሜዳው ውጪ ሳይሸነፍ ያሳልፋል ማለት ነው፡፡
 • ሊቨርፑል ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እስከዛሬ 232 ጊዜ በሁሉም ውድድሮች የተጫወቱ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትድ 88 ጊዜ እንዲሁም ሊቨርፑል 77 ጊዜ ያሸነፉ ሲሆን 67 ጊዜ አቻ ወተዋል።

 

 

 

ሊቨርፑል

 • የርገን ክሎፕ ሊቨርፑልን በአሰልጣኝነት የሚመሩበት 200ኛ ጨዋታቸው ነው፤ ይህም በቀያዮቹ ቤት 10ኛው ይህን ያህል ጨዋታ የመሩ አሰልጣኝ ያደርጋቸዋል፡፡ ነገር ግን በ200 ጨዋታዎች በርካታ ነጥቦችን በመሰብሰብ ከሁሉም ልቀው በቀዳሚነት ይቀመጣሉ፡፡
 • ሊቨርፑል በእሁዱ ጨዋታ ላይ ጎል የማያስቆጥር ከሆነ እ.ኤ.አ ከ2005 በኋላ በሉጉ በተከታታይ 3 ጨዋታዎች ላይ ጎል የማያስቆጥርበት የመጀመሪያው አጋጣሚ ይሆናል፡፡
 • ሊቨርፑል በየርገን ክሎፕ ስር ሁለት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን አስተናግዶ አያውቅም
 • ሊቨርፑል የግሪጎሪያኑ ዘመን መቁጠሪያ መሰረት አዲሱ አመት ከገባ በሀዋላ ባደረጋቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈትን ለመጨረሻ ጊዜ የቀመሰው እ.ኤ.አ በ1993 ነበር፡፡ የእሁዱን ጨዋታ የሚሸነፍ ከሆነ ከ28 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል፡፡
 • ሊቨርፑሎች በዘንድሮ የውድድር ዘመን ማግኘት ከሚገባቸው ነጥብ እስከአሁን 18 ነጥቦችን የጣሉ ሲሆን ይህም ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በሁለቱም አጋጣሚ በሙሉ የጨዋታ ጊዜ ከጣሉዋቸው ነጥቦች ይበልጣል

 

 

ማንችስተር ዩናይትድ

 • የማንቺስተር ዩናይትዶች ለመጨረሻ ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ካነሱበት እ.ኤ.አ 2012/13 የውድድር ዘመን መጠናቀቅ በሁዋላ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጠው ጨዋታ ሲጀምሩ የመጀመሪያቸው ነው፡፡
 • ማንቸስተር ዩናይትድ ያለፉትን አስራ አንድ የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፉም(W1 ፣ D2)
 • የማንቺስተር ዩናይትዱ አማካኝ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በአንድ ዓመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የወሩ ኮከብ ተጫዋች በመባል መመረጡን ተከትሎ በታሪክ ይህን ክብር ያገኘ የመጀመሪያው ተጫዋች ከሆነ በሁዋላ የሚያደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ ነው
 • ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን ውስጥ በሊጉ ባደረጋቸው የሜዳ ውጪ ጨዋታዎቸ አልተሸነፈም፡፡ የእሁዱን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ባለፈው የውድድር ዘመን ሙሉ የውድድር ጊዜ ከሜዳው ውጪ ካገኘው ድል ጋር ከወዲሁ ይስተካከላል፡፡
 • የማንቺስተር ዩናይትዶች በዘንድሮ የውድድር ዘመን ከ ታላላቆቹ 6 ክለቦች ጋር እስከአሁን 4ጊዜ የተገኛኙ ሲሆን አንዱንም ማሸነፍ አልቻሉም(2 ሽንፈት እና 2 አቻ)፡፡ በተጨማሪም እነዚህ 4 ጨዋታዎች የተደረጉት በሜዳቸው ኦልድ ትራፎርድ ሲሆን ማስቆጠር የቻሉትም 1 ጎል በፍፁም ቅጣት ምት ብቻ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.