ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ ይጀምራሉ
በ2021 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አራት ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ነጥቦች የሰበሰበው ብሔራዊ ቡድኑ ለቀጣዩ አምስተኛ የምድቡ ማጣሪያ መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ ማዳጋስካርን በሜዳው የሚገጥም ሲሆን ለዚህም ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡ ከሁለት ቀናት በኋላም ጥር 2 በጅማ ከተማ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ አሰልጣኙ በኒጀሩ የማጣሪያ ጨዋታ ከጠሯቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ አዳዲስ ዘጠኝ ተጫዋቾች በስብስቡ አካተዋል።
በጥር ወር የሚደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ ላይ የሚከወን በመሆኑ ተጫዋቾቹ ባሉበት ጅማ ዝግጅት ለማድረግ ተመርጧል። በጥር ወር መጨረሻ እና የካቲት መጀመርያ ባሉ የሊግ ጨዋታ በማይደረግባቸው ክፍት ቀናት ተጨማሪ ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚችልም ፍንጭ የሚሰጥ ነው ሲል ሶከር ኢትዮጲያ ዘግቧል