ለተሰንበት ግደይ የመጀመሪያውን ወርቅ ለሀገራ ገቢ አድርጋለች ።

ዛሬ በኦሪገን በተደረገ ተጠባቂው የሴቶች የ10 ሺ ሜትር ፍፃሜ ለተሰንበት ግዳይ ጥርሷን ነክሳ ማሸነፍ ችላለች ።

በውድድሩ ከኬኒያዊቷ ኦቢሪ እና ቼሊሞ ጠንካራ ፉክክር ቢገጥማትም ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች ። በውድድሩ ሌላው ኢትዮጵያን የወከሉት እጅጋየው ታዬ እና ቦሰና ሙላት 6ኛ እና 8ኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ ለለተሰንበት ድል በቡድን ስራ ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል ።

እጅጋየሁ ታዬ ከለተሰንበት ጋር ዙሩን በማክረር ቦሰና ሙላትም የሲፋንን ሩጫ በመከታተል ነው ዳግም የ10000 ሜትር ወርቅ ሜዳሊያን ወደ ኢትዮጵያ ያመጡት ።

በውድድሩ ከፍትኛ ግምት የተሰጣት በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሆላንዳዊዋ ሲፋን ሃሰን 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች ።

24 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለተሰንበት ግዳይ በአሜሪካ የኦሪገን አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እና ጣፋጩን የወርቅ ሜዳሊያ አምጥታለች ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.