​በከፍተኛ ሊጉ ሦስት ምድቦች የተደለደሉ ክለቦች ታውቀዋል

የከፍተኛ ሊግ ዓመታዊ ስብሰባ እና የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በሦስቱ ምድቦች የሚገኙ ክለቦችም ታውቀዋል።

በተሰረዘው የውድድር ዓመት ከነበረው የምድብ ድልድል አንድ ለውጥ የተደረገ ሲሆን ምድብ ለ ላይ የነበረው መከላከያ ወደ ምድብ ሀ፣ በምድብ ሀ የነበረው አቃቂ ቃሊቲ ደግሞ በምድብ ለ ተደልድለዋል። ይህን ተከትሎ በአቃቂ ቃሊቲ በኩል ተቃውሞ የቀረበ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና ከፍተማ ሊጉ ኮሚቴ ምላሽ ተሰጥቶበታል።

በተጨማሪም በአንድ ቦታ ውድድሩ ስለሚካሄድ በድጋሚ ሙሉ ድልድል ይካሄድ የሚል ሀሳብ ተነስቶ በመጨረሻ “አዲስ ድልድል” ወይም “በቀደመው ድልድል” መሠረት ይካሄድ የሚሉ አማራጮች ቀርበው የቀደመው ድልድል ይቀጥል የሚለው በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

ምድብ አንድ ምድብ ሁለት ምድብ ሶስት
ደደቢት  አቃቂ ቃሊቲ ደቡብ ፖሊስ
ፌዴራል ፖሊስ  ኢኮሥኮ ቂርቆስ 
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነቀምቴ ከተማ ዲላ ከተማ
መከላከያ ጅማ አባ ቡና ኢትዮጵያ መድን
ገላን ከተማ ሻሸመኔ ከተማ ባቱ ከተማ
ሶሎዳ ዓድዋ ቤንችማጂ ቡና ከምባታ ሺንሺቾ
ደሴ ከተማ ጋሞ ጨንቻ አርባምንጭ ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ
ወልዲያ ካፋ ቡና ስልጤ ወራቤ
ወሎ ኮምቦልቻ ወላይታ ሶዶ ከተማ ነጌሌ አርሲ
አክሱም ከተማ ሀላባ ከተማ ቡታጅራ ከተማ
/ ደብረብርሀ ሀምበሪቾ ዱራሜ የካ

Leave a Reply

Your email address will not be published.