​የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ከክለቡ ተሰናበቱ

ቅዱስ ጊዮርጊስን ለሦስት ዓመታት ለማሰልጠን በቅርቡ ፊርማቸውን ያኖሩት ጀርመናዊው አሰልጣኝ ኧርነስት ሚድንድሮፕ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ስላሳሰበኝና ቤተሰቦቼም በሁኔታው ግራ ስለተጋቡ በሚል ሰበብ ውሌን አፍርሼ እንድሄድ ይፈቀድልኝ ሲሉ ለቦርዱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ኧርነስት ሚደንዶርፕ የፈረሰኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ልክ የዛሬ ወር ነበር።  የቅዱስ ጊዮርጊስ የስራ አመራር ቦርድ ምንም እንኳን አሰልጣኙ ያቀረቡት ጉዳይ መሰረተ ቢስና አሳማኝ አለመሆኑን ቢገልጽላቸውም ፈቃደኛ ሆነው ስላልተገኙ ባለው የውል ስምምነት መሰረት አሰልጣኙ የሁለት ወር ደሞዛቸውን ለክለቡ ከፍለው እንዲናበቱ ወስኗል፡፡

ቅዱስ ጊወርጊስ ዋና አሰልጣኙን ኧርነስት ሚድንድሮፕ ካሰናበተ በኋላ ክለቡን በጊዜያዊነት በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ ማሂር ዴቪድስ ሃላፊነት ሰጥቷቸዋል።

ጀርመናዊው አሰልጣኝ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት በሥራቸው ከነበሩ ረዳቶች መካከል የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ያለው ማሂር ዴቪድስ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በደቡብ አፍሪካ እግርኳስ ተስፋ ሰጪ አጀማመር እያደረገ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ አሰልጣኝ ሳንቶስ ኤፍ ሲ በተባለው የደቡብ አፍሪካ ክለብ ውስጥ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ጅማሮን ካደረገ በኃላ በተመሳሳይ ማሪትዝበርግ ዩናይትድ (የሚደንዶርፕ ረዳት) እና ኤፍ ሲ ስታርስ በተባሉ ቡድኖች ውስጥ በተመሳሳይ ረዳት ሆኖ ሰርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አያክስ ሲቲ ዩዝ ፣ ኬፕ ኡመያ የተባሉ ቡድኖችም ውስጥ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ካገለገለ በኃላ ከሳምንታት በፊት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረዳት ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። አሁን ደግሞ የዋና አሰልጣኙን ስንብት ተከትሎ ክለቡን በጊዜያዊነት እንደሚመራ ተገልጿል።

በቅርቡ ረጅም ልምድ ያካበቱትን ጀርመናዊውን የቀድሞው ካይዘር ቺፍስ አሰልጣኝ ኤርነስት ሚድንዶርፕን በሦስት ዓመት ውል ካስፈረመ በኃላ በይድነቃቸው ተሰማ የማሰልጠኛ ማዕከል ልምምዱን አጠናክሮ ሲሰራ ሰንብቶ አሰልጣኙ በሀገሪቱ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ  ምክንያት በማድረግ  የመልቀቂያ  ጥያቄ በማቅረባቸው ከክለቡ ጋር መለያየታቸው  ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.