ማንቸስተር ሲቲዎች የቫሌንሲውን ፈርናን ቶሬዝን የግላቸው ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል ።
የፔፕ ጋርዲዮላዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እገዳው ከተነሳላቸው በኋላ የዝውውር መስኮቱ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
ይህንንም ተከትሎ ዘንድሮ ከማንቸስተር ሲቲ የወጣው የመሀል ሜዳውን ኳስ አቀጣጣይ ዴፊድ ሲልቫን ለመተካት የቫሌንሲውን ፈርናን ቶሬዝን የግላቸው ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል ።
ውሀ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ለ20 አመቱ ታዳጊ ለፈርናን ቶሬዝ 20ሚሊዮን ዮሮ የከፈሉ ሲሆን ወደፊት እስከ 7 ሚሊዮን ዮሮ የሚጨምሩ ይሆናል ።
ከዝውውሩም በኋላ ፈርናን ቶሬዝ ወደ ሲቲ ስለተቀላቀልኩ ደስተኛ ነኝ ሲል ተሰምቷል ።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላም በቀጣይ የቀድሞ የቼልሲ አሁን የበርንማውዝ ተከላካይ የሆነውን ናታን አኬን በ41 ሚሊዮን ዮሮ ለማስፈረም መስማማታቸው በስፋት እየተዘገበ ይገኛል ።