ኮፓ ኢታሊያ

በኮፓ ኢታሊያ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ጁቬንትስ እና ኤሲ ሚላን ተገናኝተው ካለ ምንም ግብ አቻ የተለያዩ ሲሆን በጨዋታው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፍፁም ቅጣት ምት ቢያመክንም  ጁቬንቱስ ወደ ፍፃሜ ማለፉን አረጋገጧል ።

በ ጁሴፔ ሜንዛ ስታዲየም ኤሲ ሚላን ከ አሮጊቷ ጁቬንትስ ጋር አንድ አቻ በመለያየታቸው ይታወሳል። ሆኖም ጁቬንቱሶች ከሜዳ ውጪ በማስቆጠራቸው ለፍፃሜ ከናፖሊ እና ኢንተር ሚላን አሸናፊ የሚፋለሙ ይሆናል ።

ሌላኛው ተጠባቂ የኮፓ ኢታሊያ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሸት 4:00 ናፖሊ ከ ኢንተር ሚላን የሚያገናኝ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.