የፕሮግራሞቹ ግጭት በምን ይታረቅ ይሆን?

የ2022 ኳታር የዓለም ዋንጫ ከዚህ ቀደም ከሚደረጉት ዓለም ዋንጫዎች በተለየ በኳታር ባለው አየር ሁኔታ ምክንያት በአውሮፓውያኑ የውድድር ዘመን አጋማሽ ይካሄዳል፡፡ ይህም የአብዛኞቹን ታላላቅ ሊጎች ፕሮግራም ያተራምሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለምሳሌ የ2022 የዓለም ዋንጫ በኳታር ከመጀመሩ በፊት በእንግሊዝ የሚደገሩት ፕሪሚየር ሊግ እና ሻምፒዮንሺፕ ውድድሮች ዓለም ዋንጫ ሊጀመር ዘጠኝ ቀናት ብቻ ሲቀሩት ይቋረጣሉ፡፡
ሁለቱም የውድድር አዘጋጆች አስቀድመው ባወጡት ረቂቅ ፕሮግራም የዓለም ዋንጫው ኖቬምበር 21 የሚጀመር ሲሆን ፕሪምየር ሊጉ በበኩሉ ከዓለም ዋንጫው በፊት የሚያደርገውን የመጨረሻውን መርሀ ግብር ውድድር የሚያካሂደው ኖቬምበር 12 ነው፡፡
በተጨማሪም የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ጨዋታ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን በዶሃ ውስጥ ከተካሄደ ከ14 ቀን በኋላ ፕሪሚየር ሊጉ በቦክስ ቀን 2022 እንደገና ሊጀምር ይችላል፡፡ ይህ ረቂቅ ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የተላከላቸው ሲሆን ህዳር 14 በሚካሄደው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ላይ በመወያየት ያፀድቁታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እነዚህ የፕሮግራም መመሰቃቀሎች በ9 ቀን ብሄራዊ ቡድኖች ለዓለም ዋንጫ እንዲያዘጋጁ ከተፈረደባቸው አሰልጣኞች በተጨማሪ ሁለቱን አወዳዳሪ አካላትን ያወዛግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.