ሌስተር ከዩሮፓ ሊግ ሲሰናበት ኤሲ ሚላን ከሜዳ ውጪ ባገባ በሚለው ወደ 16ቱ አለፈ
ሌስተር ከዩሮፓ ሊግ ሲሰናበት ኤሲ ሚላን ከሜዳ ውጪ ባገባ በሚለው ወደ 16ቱ አለፈ
ሌስተር በቼክ ሻምፒዮኖቹ ስላቪያ ፕራግ በሜዳው 2-0 በመሸነፍ ዩሮፓ ሊጉ ሳይጠበቅ ተሰናብቷል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ሉካስ ፕሮቮድ ስላቪያ ፕራግን በ49ኛው ደቂቃ ቀዳሚ ሲያረግ ታዳጊው አብዱላህ ሲማ በ79ኛው ደቂቃ ሌላ ጎልን አክሎ 2-0 አሸንፈው ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል፡፡
በጨዋታው ላይም በሁለቱም ጨዋታዎች እድሎችን መፍጠር አልቻልንም ነበር ስርአት እና ንቃት በተሞላበት ሁኔታ አልተከላከልንም ሁለት አናዳጅ ጎሎችንም እንዲቆጠሩብን አድርገናል የተሸለው ቡድን አሸንፏል ሲሉ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ኤሲሚላን ከሬድስታር ቤልግሬድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 1-1 ቢለያዩም በባለፋው ጨዋታ 2-2 ሲወጡ ኤሲ ሚላን ከሜዳው ውጪ ስለሆነ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረው ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡ፍራንክ ኪሲ በፍጹም ቅጣት ምት ሚላንን ቀዳሚ ቢያረግም ኤል ፋርዶ ቤን ናቡሀኔ ቤልግሬድን አቻ አድርጎ በዛው ጨዋታው አልቋል፡፡
ኦሎምፒያኮስ ፤ ሮማ ፤ ያንግ ቦይስ ፤ ሬንጀርስ ፤ ቪላርያል ፤ ሞልደ ፤ ግራናዳ ፤ ሻካታር ዶኔትስክ ፤ አያክስ ፤ ዳይናሞ ዛግሬብ እና ዳይናሞ ኪቭ ሌሎቹ ያለፉት ቡድኖች ናቸው ፡፡