የባህርዳር ስቴዲየም ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዳያስተናግድ ለሁለተኛ ጊዜ ካፍ ወስኖበታል።
▪️ለ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ኢትዮጵያ በሜዳዋ ለማድረግ የባህር ዳር ስታዲየምን በካፍ ብታስገመግምም ውድቅ ሆኖባታል፡፡
የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከያዝነው ወር መጨረሻ ጀምሮ መደረግ ይጀምራል፡፡ በምድብ 4 ከማላዊ ፣ ግብፅ እና ጊኒ ጋር የተደለደለችሁ ኢትዮጵያ በሜዳዋ ያለባትን ጨዋታ ለማከናወን የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ከቀናቶች በፊት በካፍ ባለሙያው ሚስተር ኢቫን ኪንቱ አማካኝነት ሁሉንም የሜዳውን ክፍል ፣ የመጫወቻ ሳሩን ፣ የመልበሻ ክፍሎቹን እና አጠቃላይ የስታዲየሙን ይዘት በባለሙያው አማካኝነት ያስገመገመች ቢሆንም በውጤቱ ካፍ ስታዲየሙን ሳያፀድቀው ቀርቷል።

▪️በጥቅምት ወር የካፍ የስታዲየሞች መስፈርትን ባለማሟላቱ ዕገዳ ተጥሎበት የነበረው የባህር ዳር ስታዲየም ለሁለተኛ ጊዜ የካፍ የቅጣት በትር አርፎበታል፡፡ ቀደም ባለው ዕገዳ የተነሳ ከሜዳዋ ውጪ ደቡብ አፍሪካ ላይ ከጋና አቻዋ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዋን ከዚህ ቀደም አድርጋ የነበረችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ20 ቀናት በኋላ ከማላዊ ጋር ከሜዳዋ ውጪ ከተጫወተች በኋላ በባህር ዳር ላይ ግብፅን ትገጥማለች የሚል ትልቅ ተስፋ የነበረ ቢሆንም ሜዳው ተቀባይነት አለማግኘቱን ተከትሎ በገለልተኛ ሜዳ ጨዋታዋን ማድረጓ ዕርግጥ የሆነ ሆኗል፡፡
ሚካኤል ደጀኔ።
