ተጠባቂው የአዲስ አበባ ደርቢ – ወቅታዊ መረጃ !
ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2018 የ20ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ – ተጠባቂው የአዲስ አበባ ደርቢ ሚያዝያ 18/2018 ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል።
ስለጨዋታው ተጨማሪ መረጃዎች ፦
⚽️ በጨዋታው እለት የስታዲየም በሮች ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታሉ።
⚽️ ጨዋታው በOBN የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።
⚽️ ከጨዋታው ቀደም ብሎ ከ6፡30 – 7፡20 የሁለቱ ክለቦች የቀድሞ ተጫዋቾች የወዳጅነት ጨዋታ ለ40 ደቂቃ ያደርጋሉ።
⚽️ ከክብር እንግዶች ፣ ከሁለቱ ተጋጣሚ ክለቦች ቦርድ አባላት፣ የተለየ ቪ.ቪ.አይ.ፒ(VVIP) ፍቃድ ከተሰጣቸው ተቋማት እና የሚድያ ባጅ(በተፈቀደ ቦታ) ውጪ ሌሎች የክቡር ትሪቡን ባጆች ጥቅም ላይ አይውሉም።
⚽️ ክቡር ትሪቡን በትኬት ለመግባት ሁለቱ ክለቦች ቀድመው የቆረጡት(Reserve) ትኬት እና ለሽያጭ የቀረቡ ውስን ትኬቶች ብቻ ጥቅም ላይ ይውላሉ።
⚽️ ጨዋታውን በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲታደም መላው ደጋፊ ተጋብዟል።
Via Ethiopia Premier League Share Company
✍️ ዮናታን
