ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስምምነት ፈፀሙ!
የስፖርቶች ተደራሽነትን ለማስፋት ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት ለመስራት የተስማሙ ሲሆን እ.አ.አ. በ2026 የሚጀምረው አጋርነት የስኬታማውን ውድድር ዓለም አቀፋዊ ስም የበለጠ ከፍ ያደርጋል እንዲሁም ለልጆች የሩጫ እድሎችን በእጅጉ ያሰፋል፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2026 ጀምሮ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት የበርካታ ዓመታት የአጋርነት ስምምነት ማድጋቸውን ዛሬ አሳውቋል፡፡ አጋርነቱ ባንኩ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ የነበረውን ግዙፍ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ እጅግ ተለዋዋጭ እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የሩጫ ማህበረሰቦች ወደ አንዱ እንዲያሰፋ ያግዘዋል፡፡

ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ላይ በጋራ ይሰራሉ – የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ፣ የልጆች ሩጫዎች እና ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.። ባንክ ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ውድድሮች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ደማቅ የሩጫ ባህል እይታ ለማሳደግ እና በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ንግድ አማካይነት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጋር የመሆኑ ምክንያት ተቋሙ ቀጣዩን ትውልድ ለማነሳሳት እና በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የፅናት ስፖርቶችን ለማስፋፋት ካለው ማህበረሰብ-ተኮር መርሆ የተነሳ ነው፡፡ ይህ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በስፖርት አማካይነት እድገትን የማነሳሳት እና ማህበረሰቦችን የማገዝ የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነቱን ሲያጠናክር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫን የሁሉም የህይወት ዘይቤ የማድረግ ዋነኛ ራዕይ ጋርም የተስማማ ሆኗል።
