የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን በሁለት ዙር ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ አቀና!

ከሰኔ 16-20/2025 በናይጄሪያ አቡከታ ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድን የመጀመሪያው ተጓዥ ትላኔማለዳ በ3:00 ላይ ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ ያመራ ሲሆን የኢ.አ.ፌ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአትሌቶች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት በላይነሽ ኦልጅራ ፣ የኢ.አ.ፌ ምክትል ጽ/ቤት ሃላፊ ማስተዋል ዋለልኝ ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት መልካም ምኞት በመመኘት የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድኑን ሸኝተዋል ።

ትላንት በተመሳሳይ እኩለ ሌሊትም ሁለተኛ ዙር የወጣቶች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ወደ ናይጄሪያ ተጉዟል ።የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ቅሬታ ሰሚና ዲሲፕሊን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ትእዛዙ ሞሴ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ ፣ የፌዴሬሽኑ ምክትል ጽ/ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ማስተዋል ዋለልኝ እና የፌዴሬሽኑ ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት መልካም ምኞት በመመኘት የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድኑን ሸኝተዋል ።

ኢትዮጵያ በ28 አትሌቶች በሻምፒዮናው ላይ ትወከላለች።

ምንጭ: የኢ.አ.ፌ ማህበራዊ ድረ-ገፅ

በዮናታን አየለ የቀረበ

Leave a Reply

Your email address will not be published.