ሀብትዎን በቀላሉ ማስተዳደር የሚችሉበትን ቴክኖሎጂ ተዋወቀ!
የተቀናጀ የፖስ እና ካሽ ሬጅስትር አገልግሎቶችን በአንድ ላይ መስጠት የሚያስችል አገልግሎትን ዳሸን ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ኤታ ሶሉሽንስ አስተዋውቀዋል።
ይህ “ዙሪያ” የተሰኘው ቴክኖሎጂ በባንክ ኢንዱስትሪው የመጀመሪያ የሆነ የተቀናጀ የፖስ፣ የሂሳብ ምዝገባ እና የተቋማትን ሃብት ለማስተዳደር ያስችላል ተብሏል።

በኤታ ሶሉሽንስ ኃ.የተ.የግል ማህበር የበለፀገው ይህ ቴክኖሎጂ ሁሉንም የአገር ውስጥና አለም አቀፍ ካርዶች መቀበል የሚችል ሲሆን በገቢዎች ሚኒስቴር ዕውቅና የተሰጠው የሂሳብ ምዝገባ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልፇል።

አዲሱ ፖስ ማሽን ደንበኞች በቀላሉ ክፍያ ለመፈጸም እንዲችሉ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ ሁሉንም የክፍያ መረጃዎች በአንድ ያካተተ ደረሰኝ እንዲያገኙ ይረዳልም ተብሏል።
✍️ ፈለቀ ደምሴ
