አርሰናል መሪነቱን አጠናክሯል

የሀያ አምስተኛ ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር የሊግ መርሐ አርሰናል ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጋብሬል ማርቲኔሊ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን 57 በማድረስ መሪነቱን ሲያጠናክር ሌስተር ሲቲ በ24 ነጥብ 14 ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል በተስተካካይ መርሐ ግብር ከኤቨርተን ጋር ሲገናኙ ሌስተር ሲቲ በበኩላቸው ከ ሳውዝሀምፕተን የሚገናኙ ይሆናል።

ሌላም በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታዎች

ኤቨርተን 0-2 አስቶንቪላ
ሊድስ 1-0 ሳውዛምፕተን
ዌስትሀም 4-0 ኖቲንግሃም ፎረስት

Leave a Reply

Your email address will not be published.