ማን ሲቲ ድል ቀንቶታል

በ21ኛው ሳምንት የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ከ አስቶን ቪላ ባደረጉት ጨዋታ ማን ሲቲ በሮድሪ ፣ ጉንዶጋን እና ሪያድ ማህሬዝ ጎሎች 3 ለ 1 አሸንፈዋል።

አስቶን ቪላን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ኦሊ ዋትኪንስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲዎች ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከመሪው አርሰናል በሶስት ነጥቦች ርቀው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል በተስተካካይ ጨዋታ በዕለተ ረዕቡ ይገናኛሉ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.