አርሰናል ወሳኝና ድርብ ድል አስመዘገበ
አርሰናል ወሳኝና ድርብ ድል አስመዘገበ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር እሁድ ጥር 14 ምሽት ት 1.30 የተጀመረ ጨዋታ ሲጠናቀቅ የሊጉ መሪ አርሰናል የቀድሞ ተቀናቃኙና በመጀመሪያው ዙር ያሸነፈውን ማንችስተር ዩናይትድን 3ለ2 በማሸነፍ ድርብና ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል ።
የአርሰናልን የማሸነፍያ ግብ ቡካዩ ሳካ በ53ኛው እና ኒኪታህ በ24ኛውና በጨዋታው መጠናቀቂያ 90ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥሩ ለማንችስተር ዩናይትድ ማርከስ ራሽፎርድ በ17ኛውና እና ማርቲኔዝ በ59ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል ።
👉 አርሰናል 3 – 2 ማንችስተር ዩናይትድ
⚽️⚽️ኒኪታ 24′,90′ ⚽️ራሽፎርድ 17′
⚽️ሳካ 53′ ⚽️ማርቲኔዝ 59′
ኣርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ አንደኛ ደረጃውን ሲያስከብር ማንችስተር ዩናይትድ በሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከኤቨርተን የሚጫወት ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ ክሪስቲያል ፓላስን ይገጥማል።