የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ በአዲስ አበባ ጥር 07/2015 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ በአዲስ አበባ ጥር 07/2015 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡
አስር የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተካለሉበት የአትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ የፊታችን እሁድ ጥር 07/2015 ዓ.ም. ከማለዳው 2፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ይካሄዳል ፡፡ በዚህ ኢትዮጵያ በምስታስተናግደው ጉባኤ የሪጅሉ ፕሬዝዳንት፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እንዲሁም በሪጅኑ የኮንፈዴሬሽን ኦፎ አፍሪካ አትሌቲክስ (CAA) ለካውንስል አባላት ውክልና የሚሰጥ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በዞኑ በአትሌቲክስ ልማትና እንቅስቃሴ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርትና የቀጣይ ዓመት የስራ እቅድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንደሚታወሰው እ.አ.አ. በጃንዋሪ 12/2019 በአዲስ አባባ ካፒታል ሆቴል በተደረው የሪጅኑ ስብሰባ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ የተደረገና የፌዴሬሽናችን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በምክትል ሊቀመንበርነት በመመረጣቸው እስከአሁንም ድረስ እያገለገሉ ይገኛል፡፡
እሁድ በሚደረገው ጉባኤ የኢ.ፌድሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትርና የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው እንዲሁም የኮንፈዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ (CAA) ፕሬዝደንት ሚስተር ሃማድ ካልካባ ማልቡም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ 👉የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን