ለዘመናት የእግር ኳስ ንጉስ መሆኑ የተመሠከረለት ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ በሰማንያ ሁለት ዓመቱ አረፈ።

ለዘመናት የእግር ኳስ ንጉስ መሆኑ የተመሠከረለት ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ
(ፔሌ) በሰማንያ ሁለት ዓመቱ አርፏል።

የቀድሞ የብራዚል ብሄራዊ ቡድንና ፣ በሳንቶስ እና በ ኒው ዮርክ ኮስሞስ ክለቦች ታላላቅ ገድሎችን የፈጸመው የፊት መስመር አጥቂው ባደረበት ህመም በአልበርት አንስታይን ሆስፒታል ከህዳር 20/2015ዓ.ም  ጀምሮ ህክምና ላይ ቢቆይም እነሆ ቀኑ ደርሶ ይህችን አለም ተሰናብቷል።

ሶስት የዓለም ዋንጫዎች በ1958 በ1962 እና በ1970 በማሸነፍ ሀገሩ ብራዚልን ከፍ ያደረገው የእግር ኳሱ ጀግናው ኤድሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ (ፔሌ) ህልፈት ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብና ለብራዚላውያን
ትልቅ ሀዘንን ፈጥሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.