ለታዳጊ ወጣቶች የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ማልበስ ተከለከለ

ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፕሪምየር ሊግ በትናንትናው ዕለት ታህሳስ 9/2015 መጀመሩ ይታወሳል።

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት ተጫዋቾች የነገ የኢትዮጵያ ተስፋ የሆኑ ወጣቶች እንደመሆናቸው መጠን አንዳንድ ክለቦች የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ያሉባቸው መለያዎች አልብሰው ሲያጫውቱ ተመልክተናል።

ይህ ደግሞ አግባብ ስላልሆነ እና ውድድሩ የተስፈኛ ወጣቶች ውድድር እንደመሆኑ መጠን ከ2ኛ ሳምንት ጀምሮ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ እንዲሁም የአቋማሪ ተቋማት ማስታወቂያ ያለባቸውን ማልያዎች በመልበስ ውድድር ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እያሳወቅን ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ እርምት እንዲወሰድበት ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

👉መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.