ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ሰጠ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 2ተኛ ሳምንት ተስተካካይ
ጨዋታ የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ2ተኛ ሳምንት
ተስተካካይ ጨዋታ ወላይታ ድቻን ከፋሲል ከነማ አገናኝቷል። ህዳር
25/2015 በተደረገው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ፋሲል ከነማን በዘላለም
አባተ ጎል አንድ ለ ምንም በሆነ ወጤት ረቷል።
10 ሰዓት በተደረገው ብቸኛ ጨዋታ 9 ቢጫ ካርዶች ሲመዘዙ ሁለት
ተጫዋቾች በሁለተኛ ቢጫ(በቀይ ካርድ) ከሜዳ ወጥተዋል።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት
ኮሚቴ ህዳር 26/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረገውን
ግጥሚያ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት
ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በሳምንቱ ተስተካካይ መርሃግብር ጨዋታ በተጫዋቾች ቃልኪዳን
ዘላለም(ወላይታ ድቻ) እና ኪሩቤል ሃይሉ(ፋሲል ከነማ) ሁለተኛ ቢጫ
ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ
ሜዳ የተወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ተወስኗል።
የወላይታ ድቻ ስድስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ
የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ክለቡ
የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ውሳኔ
ተላልፏል።
👉 መረጃው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አወዳዳሪ አካል ነው።