አርጀንቲና ከሰላሳ ስድሽንፈት ዋታዎች በኋላ በሳውድ አረቢያ ተሸነፈች
በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ አርጀንቲና በሳውዲ አረቢያ 2ለ1 ተሸንፋለች ።
አርጀንቲና ከጨዋታው አስቀድሞ ከፍተኛ ግምት ቢሰጣትም በሳውዲ አረብያ ድንገተኛ ሽንፈት ገጥሟታል ።
አርጀንቲናዎች በኮኮባቸው ሊዮኔል ሜሲ ⚽️በ10 ኛው ደቂቃ ግብ 1 ለ 0 መምራት ቢችሉም በሁለተኛው አጋማሽ አል ሼህሪ ⚽️በ48 ኛው ደቂቃ እና ሳውድ አል ዶውሰሪ ⚽️በ53 ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት 2 ግብ ሳውዲ አረቢያ 2 ለ 1 እንድታሸንፍ አስችለዋታል ።
በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታዎች ቅዳሜ ፖላንድ ከ ሳውዲ አረቢያ እና አርጀንቲና ከ ሜክሲኮ ጋር የሚገናኙ ይሆናል ።