አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዛሬው ጨዋታ አስቀድሞ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።

▪️ከካሜሮን ጋር ባደረግነው ጨዋታ ቀድመን ማግባት ችለን ነበር። ያለኛ ጥሩ ስንቅ ነው ግን ብዙም ሳይቆይ ጎል አስተናገድን ምንም እንኳን በመልሶ ማሳያ ስንመለከተው ጎሉ ንፁህ ጎል እና አጨቃጫቂ ቢሆንም ማለት ነው። ግን ጨዋታው ከእጃችን እንዳይወጣ የተቻላቸውን ሞክረዋል እስከ እረፍት የተወሰኑ የግብ እድሎችን መፍጠር ችለን ነበር። ከእረፍት በኋላ በተከታታይ የተቆጠሩብን ግቦች ልጆቹ ላይ አለመረጋጋትንእና ተጫዋቾቹ የመንፈስ ረብሾብናል ግን አሁን ጥሩ መንፈስ ላይ ነው ምንገኘው ያለችውን እንጥፍጣፊ እድል ለመጠቀም ተዘጋጅተናል።

▪️በጤና በኩል ሁሉም የቡድኑ አባላት ከኮቪድ ነፃ ናቸው ከሽመልስ በቀለ ውጪ ማለት ነው ሽመልስ በቀለ አሁንም ጉዳት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። አቡበከር ናስርም መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል።ከጨዋታው ያርቀዋል ወይስ አያርቀውም እሚለውን እርግጠኛ አይደለሁም ብለዋል አሰልጣኙ።

▪️ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ማብራሪያ እና ምላሽ ሰተውበታል።ቡድኑ ከእረፍት መልስ በአካል ደክመው ታይተዋል ለምን ይሆን ለተባለው ጥያቄ?

ውበቱ እንዲህ ብለዋል 🗣 2 እና 3 ጎል ሲገባ እየመራን ስለተመራን ዳገት አድርገው ነገሮችን ማሰባቸው እና ልምድም ስለሌላቸው ማለት ነው። ስለዚህ Mentally በዛ መልኩ ስላሰቡ እንጂ ደክመው ነበር ወይም physically fit አልነበሩም ለማለት ይከብዳል ብለዋል። አያይዘውም የካሜሩን ጨዋታ ላይ offensively እድል በመፍጠር ረገድ በተለይ የመጀመሪያው አጋማሽ በጣም ጥሩ ነበርን ግን መከላከሉ ላይ ብዙ ክፍተቶች ነበሩብን እሱ ግልፆ ነበር።

▪️ከውድድሩ መሰናበት እንደ ውድቀት ታየዋለህ ተብሎ ለተነሳው ጥያቄም?
🗣 የተጋነነ እቅድ ይዘን አልነበረም ወደዚህ መድረክ የመጣነው ግን የ cape’verde ጨዋታ ያየኘው ቀይ ካርድ ነገሮችን እና እቅዳችንን ነበር ያበላሸው ግን ጌሙ አላለቀም ከ ቡርኪናፋሶው ጋር የተሻለ ነገር አሳይተን በተሻለ መጠን ደግሞ ውጤት ይዘን ለመውጣት እንሞክራለን ብሏል አሰልጣኝ ውበቱ አባተ።

▪️እስካሁን ካደረካቸው ጨዋታዎች እንደገና ቢደገሙ እና የተሳሳተ ውሳኔ ወስኛለሁ እናም ይቆጨኛል ብለህ ምትለው ነገር አለ ወይ? ተብሎ ለቀረበለት የመጨረሻ ጥያቄ?

🗣 ሁለቱም ጨዋታዎች ቢደገሙ እንዳይጠላ ምክንያቱም ለሚጠብቀን ህዝብ 1 ነጥብ እንኳን እናሳካለን ብዬ ስለማምን ነው። የሚቆጨኝ እና የተሳሳተ ውሳኔ የምለው ነገር የካሜሩን ጨዋታ ላይ ፉልባኮቹን ማለትም ሱሌማን ሀሚድ እና ረመዳን የሱፍ ላይ ያለውን ጫና ሚቀንስ እና ሊያግዝ ሚችል ተጫዋች አለማስገባቴ ይቆጨኛል ግን እነሱም(ካሜሮን ብሄራዊ ቡድን) ቅያሪዎችን እስክንፈፅም ድረስ እድል አልሰጡንም።

የዛሬውን ጨዋታ ‘ይቻላል’ የሚለውን መንፈስ ይዘን ነው ወደ-ሜዳ የምንገባው። እናሸንፋለን ማለት እናልፋለን ማለት አይደለም ግን ለማሸነፍ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው አሰላለፍ ላይ የቡርኪናፋሶው አጨዋወት ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠነኛ ቅያሪዎች ልናደርግ እንችላለን ሲሉ ሀሳባቸውን አካፍለዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.