በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ኢኳዶር አዘጋጇን ሀገር ረታለች

የ2022ቱ የኳታር አለም ዋንጫ ጅማሮውን አግኝቷል ።

በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ኢኳዶር አዘጋጇን ሀገር ረታለች

የ 2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ዛሬ ሲጀምር አዘጋጇ ሀገር ኳታር በኢኳዶር 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች ። ለኢኳዶር የማሸነፊያ ግቦቹን ኢነር ቫሌንሽያ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል።

ውጤቱንም ተከትሎ ኳታር በአለም ዋንጫ ታሪክ አዘጋጅ ሆኗ በመክፈቻው ጨዋታ የተሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

ኳታር በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ በመጪው አርብ ሴኔጋልን ስትገጥም ኢኳዶር በበኩሏ ኔዘርላንድን የምትገጥም ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.