ቼልሲ ሽንፈተን ሲያስተናግድ ቶተንሀም ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል ።
ቼልሲ ሽንፈተን ሲያስተናግድ ቶተንሀም ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል ።
በአስራ አራተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ በብራይተን ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግዷል።
አራት ጎሎች ትሮሳርድ ፣ ፓስካል ግሮብ እንዲሁም ሎፍተስ ቼክ እና ቻሎባህ በራሳቸዉ መረብ ላይ አስቆጥረው የምዕራብ ለንደኑን ቼልሲ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ።
ቼልሲን ከሽንፈት ያላዳነች ብቸኛ ጎል ካይ ሀቨርትዝ ሲያስቆጥር አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር ቼልሲን ከተረከቡ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈታቸዉን በቀድሞ ክለባቸዉ ብራይተን አስተናግደዋል ።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ አርሰናል እንዲሁም ብራይትን ከ ዎልቭስ የሚገናኙ ይሆናል።
ሌላ በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ቶተንሀም ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል ።
የአሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴዎቹ ቶተንሀሞች 2 ለ 0 ከመመራት ተነስተው አዲስ አዳጊውን በርንማውዝ 3 ለ 2 መርታት ችለዋል ።
ለቶተንሀሞች ሴሴኞ ፣ ዴቪስ እና ቤንታናኩር ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ለበርንማውዝ ደግሞ ሞር 2 ግቦች አስቆጥሯል ።
ሌሎች በተመሳሳይ ሰዓት የተደረጉ መርሀ ግብሮች
ብሬንትፎርድ 1-1 ወልቭስ
ኒውካስትል 4-0 አስቶን ቪላ
ክሪስታል ፓላስ 1-0 ሳውዛምፕተን