ኢትዮጵያ መድን መቻልን 2 ለ 1 ረቷል።
ዛሬ 10:00 ሰዓት በተደረገዉ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን መቻልን 2 ለ 1 ረቷል።
ሁለቱን የኢትዮጵያ መድን የማሸነፊያ ጎሎች በ20ኛዉ ደቂቃ አህመድ ረሺድ በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም በ57ኛዉ ደቂቃ ባሲሩ ኡመር አስቆጥረዋል።
መቻልን ከሽንፈት ያልታደገች ጎል በሀይሉ ግርማ በ28ኛዉ ደቂቃ አስቆጥሯል።
በቀጣዩ 6ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን አርብ ጥቅምት 25 9:00 ሰዓት ላይ ከባህርዳር ከነማ የሚጫወት ሲሆን መቻል ቅዳሜ ጥቅምት 26 09:00 ሰዓት ላይ ከወላይታ ጋር ይጫወታል።
