ባህርዳር ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
ዛሬ 7:00 ሰዓት በተደረገ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ባህርዳር ከነማ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
የባህርዳር ከነማን የማሸነፊያ ጎሎች ኦሴ ማዉሊ በ28ኛዉ ደቂቃ እንዲሁም ፉአድ ፈረጃ በ66ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።
በቀጣዩ 6ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ባህርዳር ከነማ አርብ ጥቅምት 25 9:00 ሰዓት ላይ ከኢትዮጵያ መድን የሚጫወት ሲሆን ለገጣፎ ለገዳዲ ሰኞ ጥቅምት 28 12:00 ሰዓት ላይ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ይጫወታል።