ኢትዮጵያ ቡናና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሸነፉ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ዉሎ ሁለት ጨዋታዎች የተስተናገዱ ሲሆን 7:00 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና መስፍን ታፈሰ በ20ኛዉ ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ማሸነፍ ችሏል።

በአምስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማክሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 7:00 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከወልቂጤ ከተማ የሚጫወት ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ሀሙስ ጥቅምት 17: 10:00 ሰዓት ላይ ከአርባ ምንጭ ከተማ ይጫወታል።በእለቱ ሁለተኛ ጨዋታ 10:00 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለገጣፎ ለገዳዲን 3 ለ 0 በሆነ ዉጤት ረቷል። ሶስቱም ጎሎች የተቆጠሩት ከእረፍት በፊት ሲሆን ሄኖክ አየለ በ22ኛዉ ደቂቃ አብነት ደምሴ በ29 እንዲሁም ምንያህል ተሾመ በ44ኛዉ ደቂቃ ኳስ ከመረብ በማሳረፍ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸናፊ ማድረግ የቻሉ ተጫዋቾች ናቸዉ።

በአምስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኞ ጥቅምት 14 10:00 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከአዳማ ከተማ ያገናኛል። ለገጣፎ ለገዳዲ ረቡዕ ጥቅምት 16 7:00 ሰዓት ላይ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ጨዋታዉን ያደርጋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.