ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን በመርታት ግስጋሴውን ቀጥሏል።

በአራተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን በመርታት ግስጋሴውን ቀጥሏል።
የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ ሲጠናቀቅ ከረፍት መልስ
51ኛው ደቂቃ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቀዳሚ መሆን የቻለበትን ግብ እስማኤል ኦሮ አጎሮ ሲያስቆጥር በ66ኛው ደቂቃ ላይ ዳዋ ሆቴሳ አዳማን አንድ አቻ ማድረግ ቢችልም ፈረሰኞቹ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከግቡ በዃላ ከፈተኛ ጫና ፈጥረው በማጥቃት በ88ተኛው ደቃቃ የአዳማ ከተማው የመሀል ተከላካይ አዲሱ በአማኑኤል ላይ በሰራው ጥፋት የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት እስማኤል ኦሮ አጎሮ ለራሱና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡፡ኦሮ አጎሮ በአራት ጨዋታ ያስቆጠራቸውን ግቦች ስምንት በማድረስ የኮኮብ ግብ አግቢነቱንም መምራት ቾሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.