የባሎንዶር አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ

የወንዶች ባሎንዶር አሸናፊ  እንደተጠበቀው ሆኗል

👉የ 2022 የአመቱ ምርጥ የወንድ እግር ኳስ ተጫዋች በመባል ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ካሪም ቤንዜማ ከቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ዚነዲን ዚዳን እጅ ሽልማቱን ተቀብሏል።

👉ፈረንሳዊው  ካሪም ቤንዜማ ከሀገሩ ልጆች ራይሞንድ ኮፓ ፣ ሜሼል ፕላቲኒ ፣ ጂያን ፔር ፓፒን እና ዚነዲን ዚዳንን ቀጥሎ ባሎንዶርን ማሸነፍ የቻለ ተጫዋች ሆኗል።ለዚህም መነሻው አርባ አራት ጎሎችን  ሲያስቆጥር ሪያል ማድሪድን በላሊጋ እና ሻምፒየንስ ሊግ እንዲያሸንፍ አስችሎታል ። እሱን በመከተል ሳድዮ ማኔ 2ኛ  ኬቨን ዴብሮይነ 3ኛ እንዲሁም ሮበርት ሊዋንዶውስኪ  4ኛ  ሆነዋል

ካሪም ቤንዜማ  ከባድ ልምምዴን ጠንክሬ እሰራ ነበር ዚነዲን ዚዳን እና ሮናልዶን እያየሁ ማደጌም ጠቅሞኛል ሁሉንም አጋሮቼን አሰልጣኞቼን ፣ ሪያል ማድሪድን አባላትን በሙሉ አመሠግናለሁ በማለት ደስታውን ገልጿል።

 

👉የ ባሎን ዶር የሴቶች አሸናፊ ስፔናዊቷ የባርሴሎናዋ የአጥቂ አማካይ ተጫዋች አሌክሲያ ፑቴያስ ሆናለች ፑቴያስ የሴቶች የባሎን ዶር ሽልማትን ባለፈው አመትም ማሸነፏ ይታወቃል ።

👉ሴኔጋላዊው ሳድዮ ማኔ የሶክራተስ የሽልማት ዘርፍ አሸናፊ መሆኑ ተገልጿል።

ሳድዮ ማኔ ከእግር ኳስ ውጪ በሚያደርጋቸው ሰብአዊ ስራዎቹ እና በጎ አድርጎቱ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ ሆኗል።

 

👉ስፔናዊው የ ባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቪ የ ኮፓ ትሮፊ አሸናፊ ሆኖ ሲያጠናቅቅ እሱን መከተል

2ኛ. ጋቪ ( ባርሴሎና )
3ኛ ኤድዋርድ ካማቪንጋ ( ሪያል ማድሪድ  )
4ኛ. ጀማል ሙሴይላ ( ባየር ሙኒክ )

 

👉በ ውድድር አመቱ ከ 21 አመት በታች ድንቅ ብቃታቸውን ላሳዩ ታዳጊ ተጫዋቾች ( Kopa Trophy ) አሸናፊ የባርሴሎናው ታዳጊ የመሐል ሜዳ ተጫዋች #ጋቪ ሆኗል ።

👉የአመቱ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች የባርሴሎና የፊት መስመር አጥቂ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ሆኗል ።

 

👉የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ
የሪያል ማድሪድ እና የቤልጅዬሙ ቲቡዋ ኩርቱዋ ሆኗል ።

 

የአመቱ ምርጥ ክለብ ማንችስተር_ሲቲ ሆኗል።

ሊቨርፑል እና ሪያል ማድሪድ ተከታዮቹን ደረጃዎች በመያዝ አጠናቀዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published.