ሰባት ጎል የተቆጠረበት የሀዋሳ ከተማና የወልቂጤ ከተማ ጨዋታ

የአራተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማና ወልቂጤ ከተማን ሲያገናኝ ሀዋሳ ከተማ ጨዋታው በተጀመረ በ8ኛው ደቂቃ ኤፍሬም አሻሞ ባስቆጠረው ግብ መምራት የጀመሩ ሲሆን
በ16ኛው ደቂቃ ሙጂብ ቃሲም ሁለተኛ ግብ በማስቆጠር ሀዋሳዎችን ሁለት ለዜሮ በመምራት ያስቻለ ሲሆን
ወልቂጤዎች በ31ኛው ደቂቃ ብዙዓየው ሰይፈ ከርቀት ባስቆጠራት ግብ ወልቂጤዎችን ወደጨዋታው የመለሰ ሲሆን
የመጀመሪያው ግማሽ ክፍለጊዜ ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀር ጌታነህ ከበደ ሁለተኛ ጎል አስቆጥሮ በሁለት አቻ ወደመልበሻ አምርተዋል

ከረፍት መልስ በ53ኛው ደቂቃ ሙጂብ ቃሲም ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ሦስተኛ ጎል አስቆጥሯል ።በ75ኛው ደቂቃ ላይ ሙጂብ ቃሲም በግንባሩ በመግጨት ግሩም ጎል በማስቆጠር ሀትሪክ በመስራት የሀዋሳዎችን መሪነት ያጠናከረ ሲሆን
90 ደቂቃው ተጠናቆ በተጨማሪ ደቂቃ የሀዋሳ ተከላካይ ኳስ በእጅ በመንካቱ ፍፁም ቅጣት ለወልቂጤ ከተማ በመሠጠቱ ጌታነህ ከበደ ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ሦስተኛ ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በሀዋሳ 4 ለ3 አሸናፊነት ተጠናቋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.