ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍራካ ዋንጫ ካስገኙት አንዱና ዋነኛው ጀግና አረፈ።

ብቸኛውን የአፍራካ ዋንጫ ካስገኙት አንዱና ዋነኛው ጀግና አረፈ።

<<ጥር 13 ቀን 1954 ዓ.ም ኢትዮጵያና ግብፅ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ በግብፅ 1ለ0 መሪነት እረፍት ወጡ፡፡ ከእረፍት በኋላ ተክሌ ባስቆጠራት ግብ አቻ ሆኑ፤ ግብፆች ሁለተኛውን ግብ አስቆጥረው መሩ፤ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃ ሲቀረው ሉቻኖ ቫሳሎ ሁለተኛዋን ግብ አስቆጥሮ 2ለ2 በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡ ይህ ውጤታቸው ደግሞ ተጨማሪ 30 ደቂቃ እንዲጫወቱ አደረጋቸው፡፡ በጭማሪው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሦስተኛዋን ግብ ኢታሎ ቫሳሎ የመጨረሻዋን ወሳኝ አራተኛ ግብ ደግሞ መንግስቱ ወርቁ በማስቆጠር ኢትዮጵያ ግብፅን 4ለ2 አሸንፋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ለመሆን ችሏል፡፡ >> ከኢትዮጵያ እግርኳ ጉዞ መጸሀፍ የተወሰደ

ኢትዮጵያውያን በ90 ደቂቃ ከመሸነፍ ያዳነቸውን ወሳኝ ጎል ያስቆጠረውና የ3ኛው አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ እንድትሆን ካደረጉ ጀግኖች አንዱ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች እና ሉቺያኖ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የሉቺያኖ ቫሳሎ ስርዓተ ቀብር በነገው ዕለት በጣልያኗ ሊዶ ከተማ ቅድስት ሞኒካ ቤተ – ክርስቲያን የሚፈፀም ይሆናል።

ኢትዮጵያን ስፖርት ለመላው እግርኳስ አፍቃሪውች መጽናናትን ይመኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.