የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባ

የአፋር ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለስራ አስፈጻሚ እንዲወዳደሩ ያቀረብናቸው የአቶ አሊሚራህ ያለአግባብ ውድቅ ሆነውብናል እና ጉባኤው እንዲወያይበትና ውሳኔ እንዲሰጠን ብለው ጠይቀዋል ጉባኤውም አቶ አሊሚራህ አዲሱ የጉባኤው አባል እንዲሆን የቀረበው ጥያቄ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።

የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤው ጎንደር ላይ እንዲሆን ተወስኖ ወደአዲስ አበባ እንዲቀየር መደረጉ አግባብ የለውም ጉባኤው እንዲወያይበትና ውሳኔ እንዲሰጠው ብለው ጠይቀዋል ጥያቄው አግባብነት እንደሌለው አቶ ኢሳያስ ጅራ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ይህም አግባብ አይደለም በማለት የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተወካይ በመቃወም ማብራሪያ መስጠት ካስፈለገ ለኛም እድሉ ይሰጠን ብለው የጠየቁ ሲሆን በቀጥታ ድምጽ እንዲሰጥበት ተደርጎ ጉባኤው ለውይይት እንዳይቀርብ በድምጽ ብልጫ ወስኗል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በባሕል እና ስፖርት ሚንስቴሩ ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የመክፈቻ ንግግር ከተከፈተ በኋላ የጉባኤው አጀንዳዎች ቀርበው ፀድቀው የፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ሥራዎችን አብራርተዋል። እንዲሁም የፋይናንስ ሀላፊው አቶ ነብዩ ደመሴ የፋይናንስ ሪፖርት አቅርበዋል። አቶ ነብዩ ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ 235,783,534.50 ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ገቢ አድርጎ 252,805,711.33 ወጪ መደረጉን ይፋ አድርገዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.