አመቱን በድል የጀመሩት መድፈኞች
አመቱን በድል የጀመሩት መድፈኞ
መድፈኞቹ በ2022/23 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል ።
የ2022/23 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ከክርስቲያል ፓላስ ጋር ያደረጉት የሰሜን ለንደኖቹ አርሰናሎች ሁለት ለ ዜሮ በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ።
ጨዋታው እንደተጀመረ አርሰናሎች ጫና ፈጥረው ተጫውተው በ20 ኛው ደቂቃ በጋብሬል ማርትሌኒ ግብ መሪ መሆን ቻሉ ። ዘግይተው ቢሆን ወደ ጨዋታው የገቡት ክርስቲያል ፖላሶች በኢዜ እና በኤድዋርድ ያለቀለላቸው እድሎች ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ።
ከእረፍት መልስ የአሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ ቡድን ክርስቲያል ፓላስ ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም በጨዋታው መገባደጃ ላይ ቡካዮ ሳካ የመታውን ኳስ ማርክ ጉሂ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥሮ ጨዋታው በአርሰናሎች 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋቋል ።
በመድፈኞቹ አርሰናሎች በኩል አዳዲስ ፈራሚዎቻቸው ዚንቼንኮ እና ጋብሬል ጀሰሱ አሪፍ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ዚንቼንኮም የመጀመሪያው ጎል እንዲቆጠር ለማርቲሌኒ አመቻችቶ አቀብሏል ።
ሌላኛው ተጠባቂው ተጫዋች ዊሊያም ሳሊባ በመጀመሪያው የአርሰናል ጨዋታው የጨዋታው ኮኮብ በመባል ተመርጧል ።
ሀሳብ አስተያየትዎን ይለግሱን
በፈቃደኝነት ላይክ ሼር ኮሜንት ያድርጉ እናመሰግናለን ።
Ananiya Feleke