በኮሎንቢያ ካሊ ኢትዮጵያዊው ጀግና መልኬነህ ሁለተኛውን ወርቅ አስገኘ
እንኳን ደስ አለን
አሁን በተጠናቀቀ በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የ3000ሜ. የወንዶች ፍፃሜ ወድድር ኢትዮጵያውያኑ ጀግና መልኬነህ አዘዘ 7.44.06 በድንቅ ሁኔታ ተስፈንጥሮ በመውጣት በሰፊ ርቀት በመቅደም ለሀገሩ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ገቢ አድርጓል።
ድርባ ግርማ 7.50.63 አራተኛ በመሆን የዲፕሎማ አሸናፊ ሆኗል።
ኬኒያውያኑ ፍሌክስ እና ኤድዊን 7.47.86.
7.49.82 በመግባት ለሀገራቸው ኬኒያ የብርና ነሀስ ሜዳልያ በማስገኘት ሀገራቸውን ከፍ ማድረግ ችለዋል።
ምስል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
