ሳድዮ ማኔ በመጨረሻም አሸናፊ ሆኗል

ሳድዮ ማኔ የ2022 የካፍ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል ።
በዘንድሮ የዝውውር መስኮት ሊቨርፑልን ለቆ ወደ ወደ ጀርመኑ ክለብ ባየርን ሙኒክ ያቀናው ማኔ በውድድር ዓመቱ ከክለቡ ሊቨርፑል ጋር የኤፍ ኤ ካፕ እና የካራባዎ ካፕን ማሸነፉ ይታወሳል ። ከሀገሩ ሴኔጋል ጋር ደግሞ የአፍሪካ ዋንጫ ማሳካት ችሏል ።
ማኔ በእጩነት የቀድሞውን የቡድን አጋሩ ሞሀመድ ሳላህን እና የሀገሩን ልጅ ኤድዋርድ ሜንዲን በመብለጥ ነው የአመቱ የአፍሪካ ኮኮብ መባል የቻለው ።
በሌላ የሽልማት ዘርፍ
👉 የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች = ናይጄሪያዊዋ የባርሴሎና ተጫዋች አሲሳ ኦሾላ
👉 በዓመቱ ምርጥ የወንዶች አሠልጣኝ = የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አልዮ ሲሴ
👉 የሴቶች የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ = ደቡብ አፍሪካዊቷ ደሲረ ኤልስ
👉 የዓመቱ ምርጥ ጎል = የሴኔጋላዊው ፔፔ ኦሱማኔ ጎል
👉 የዓመቱ ምርጥ ብሄራዊ ቡድን = የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን
👉 የዓመቱ የወንዶች ምርጥ ወጣት ተጫዋች = ሴኔጋላዊው ፔፔ ማታር
👉 የአመቱ የሴቶች ምርጥ ወጣት ተጫዋች ኤቭሊን ባዱ

Leave a Reply

Your email address will not be published.