በማራዶና ሞት ምክንያት የህክምና ባለሙያዎቹ ለፍርድ ሊቀርቡ ነው ።

አርጀቲናዊው የቀድሞ ድንቅ እግር ኳሰኛ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በ2020 በቦነሳይረስ ከተማ በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት መለየት በርካታ የእግር ኳስ ቤተሰቡንም ሆነ አርጀንቲናዊያንን ልብ የሰበረ ነበር ።
የማራዶና ሞት የህክምና ስህተት የነበረበት መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ማረጋገጡን ተከትሎ ነው የህክምናውን ቡድን በግድያ ወንጀል በችሎት እንዲታይ የተወሰነው ።
ማራዶና በሞተ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር የአርጀቲና አቃቢ ህግ በህክምናው ቡድን ላይ ምርመራ የከፈተው ።
የህክምናው ቡድን በቸልተኝነት በተደረገ የግድያ ወንጀል ነው ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርቡት ። በአርጀንቲና ወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሠረት ወንጀሉ ከስምንት እስከ ሀያ አምስት እስራት ያስቀጣል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.