የኮንፈረንስ ሉግ የፍፃሜ ጨዋታ።

▪️የአውሮፓ ጨዋታዎች አወዳዳሪ አካል (ዩ.ኤፋ) ዘንድሮ የጀመረውና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የአውሮፓ የኮንፈረንስ ሊግ የፍፃሜውን ጨዋታ በሮማ እና ፌይኖርድ መካከል በ አልቤኒያ ቲራና ኮምቤታሬ ስቴዲየም ፍፃሜውን አግኝቷል።

▪️ የመጀመሪያው አጋማሽ በሙከራዎች ያልታጀበ ፣ ቀዝቀዝ ያለ እንዲሁም ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደረገ ጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች ተንፀባርቋል ግን 30ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ ከክሪስታንቴ የተሻገረለትን ኳስ በሚገባ በመጠቀም ኒኮሎ ዛኒዮሎ ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ቻለ። በሩብ ፍፃሜው ጨዋታ ከ ኖርዌዩ ቦድ/ግሊምት ጋር ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ጎል ማስቆጠር ያልቻለው ኒኮሎ ዛኒዮሎ በፍፃሜው ቡድኑን ቀዳሚ ያደረገች ወሳኟን ግብ አስገኝቷል። የአውሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ግብ ማስቆጠረ የቻለ በእድሜ ትንሹ ጣልያናዊም መሆን ችሏል። ሮማም ለእረፍት 1-0 በሆነ ውጤት እየመራ መውጣት ችሏል።

▪️በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሩ አንስቶ በአርኔ ስሎት የሚመሩት ፌይኖርዶች በተደጋጋሚ በአማካዩ ጉስ ቲል እንዲሁም በማላሲያ አማካኝነት በተደጋጋሚ አቻ ለመሆን ያደረጉት ጥረት በግብ ጠባቂው ሩዊ ፓትሪሲዮ ከሽፏል። ውጤቱም 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህም መሰረት ሮማ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል።

▪️የ59 አመቱ ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆም በክለብ ደረጃም በግላቸውም አዲስ ታሪክ ፆፈዋል። ሮማን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ ላይ የዋንጫ ባለበቤት ከማድረጋቸውም በተጨማሪ በግል ደግሞ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 2003 ከፖርቶ ጋር ፣ 2010 ከኢንተርሚላን ጋር በማንሳት ከ5 አመት በፊት ደግሞ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የዩሮፓ ሊግን በማንሳት እንዲሁም ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ በማሸነፍ የመጀመሪያው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.